SBS Amharic - ኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ

SBS Amharic

Listen to interviews, features and community stories from the SBS Radio Amharic program, including news from Australia and around the world. - የአውስትራሊያና ዓለም አቀፍ ዜናዎችን አካትቶ፤ ቃለ ምልልሶችን፣ ዘገባዎችንና የማኅበረሰብ ታሪኮችን ከኤስ.ቢ.ኤስ አማርኛ ፕሮግራም ያድምጡ።

  • 10 minutes 57 seconds
    በትግራይ ክልል ለሠራዊት ብተናና መልሶ ማቋቋም ሥራ የሚውል ከዓለም አቀፍ አጋር አካላት 60 ሚሊዮን ዶላር፤ ከፌዴራል መንግሥቱ አንድ ቢሊየን ብር መመደቡ ተገለጠ
    የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካይሮ - ግብፅ በተካሔደው 56ኛው የአፍሪካ አየር መንገዶች ማኅበር አጠቃላይ ስብሰባ ላይ በዓለም አቀፍ አገልግሎት ዘርፍ "የዓመቱ ምርጥ አየር መንገድ" ሆኖ ለስምንተኛ ጊዜያት ሽልማት ተቀዳጀ
    24 November 2024, 10:41 pm
  • 11 minutes 42 seconds
    "በደቡብ አውስትራሊያ ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ዘንድ ባካሔድነው ጥናት የዕንቅልፍ ማጣት ችግር 40 ፐርሰንት ነው" ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ
    ዶ/ር ዮሐንስ አዳማ መላኩ፤ በፍሊንደርስ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና መካነ ተቋም ገዲብ ተመራማሪ፤ በተለይ በአደላይድ - ደቡብ አውስትራሊያ ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ነዋሪዎችን በተመለከተ በቡድን ስላካሔዱት የዕንቅልፍና አመጋገብ ጥናታዊ ምርምር ዓላማና ግኝቶችን ነቅሰው ያስረዳሉ። በደቡብ አውስትራሊያ የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ማኅበር ጋር በመተባበር ሂደትና ውጤቱንም ቅዳሜ ኖቬምበር 30 / ሕዳር 21 ለማኅበረሰቡ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ እንደምን ለውይይት እንደሚበቃ ይገልጣሉ።
    24 November 2024, 9:20 pm
  • 8 minutes 25 seconds
    የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚደንት ጌታቸው ረዳ ከኤርትራ ጋር ሥራን መፍጠር እንደሚፈልጉና ዳግም ጦርነት ማካሔድ እንደማያሻ አመላከቱ
    ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ደኅንነት ስጋት መሆኑ እስከሚያበቃ ድረስ ኢትዮጵያ አልሻባብን ከማዳከም ተግባር እንደማትገታ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ
    21 November 2024, 12:03 am
  • 18 minutes 19 seconds
    "መንገደኞች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ላይ የሚያገኙት መስተንግዶ ብቻ አይደለም፤ ባሕልም ነው" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ
    ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ የአየር መንገዱን ሁነኛ ትልሞችና ትግበራዎች ያመላክታሉ።
    20 November 2024, 7:20 am
  • 13 minutes 24 seconds
    "ርዕይ 2035 ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢያንስ ወደ ሶስት የአውስትራሊያ ከተሞች ለመብረር ወስኗል" ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ
    ኢንጂነር ተሊላ ደሬሳ ጉተማ የሲንጋፖር፣ አውስትራሊያና ኒውዝላንድ ቀጣና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስኪያጅ፤ ስለ አውስትራሊያ የሥራ ጉብኝታቸው ተልዕኮና የአየር መንገዱን ውጥኖች አንስተው ያስረዳሉ።
    20 November 2024, 7:03 am
  • 10 minutes 58 seconds
    "የተቃውሞ ሰልፍ ያካሔዱ ወገኖች በአማራ ክልል ተንቃሳቃሽ የሆኑ ኃይሎች ወጥ አመራር ፈጥረው ለውይይትና ድርድር ዝግጁ እንዲሆኑ ተፅዕኖ መፍጠር አለባቸው" አምባሳደር ሃደራ
    በአውስትራሊያና ኒውዝላንድ የኢትዮጵያ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሃደራ አበራ አድማሱ፤ በዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልና በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪነት በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ያካሔዱትን የተቃውሞ ሰልፍ ተከትሎ የተነሱ ሀገራዊ ጉዳዮችን አስመልክተው የኢፌዴሪ መንግሥትን አተያይ ያንፀባርቃሉ።
    18 November 2024, 3:13 pm
  • 11 minutes 48 seconds
    በናሙናነት ወደ ውጪ ሀገራት የሚላኩ ማዕድናት ወደ ሀገር ውስጥ እንደማይመለሱ በሕዝብ ምክር ቤት ተነገረ
    የአፋር ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ከትጥቅ ትግል ወጥቻለሁ አለ
    18 November 2024, 1:48 pm
  • 15 minutes 28 seconds
    "በአማራ ክልል የድሮን ጥቃትና ጦርነት በአስቸኳይ እንዲቆም የአውስትራሊያ መንግሥት በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርግ እንጠይቃለን" አቶ ግርማ አካሉ
    አቶ ግርማ አካሉ፤ የዓለም አቀፍ አማራ ግብረ ኃይልን በሜልበርን የአማራ ኅብረት አስተባባሪ፣ ወ/ሮ ትዕግሥት አበረ፤ የተቃውሞ ሰልፍ ተሳታፊና አቶ ዳዊት ይኩኑ፤ በሜልበርን ከተማ የቪክቶሪያ ፓርላማና ፌዴሬሽን አደባባይ ስለ አካሔዱት የተቃውሞ ሰልፍ ዓላማ ያስረዳሉ።
    18 November 2024, 1:20 pm
  • 14 minutes 20 seconds
    "በዘር መተዋወቅ ጥላቻን ነው ያመጣው፤ ወገን እንጂ ዘር አያስመካም፤ ከየትኛውም ዘር ሁኑ አንድ ወገን ነን" መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ
    መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ፤ በሜልበርን ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ለሕትመት አብቅተው እሑድ ሕዳር 8 / ኖቬምበር 17 ለምርቃት ስላሰናዱት "እኔ ማነኝ?" መፅሐፋቸው ዋነኛ ጭብጦች ይናገራሉ።
    13 November 2024, 11:55 pm
  • 16 minutes 12 seconds
    "ማንነታችንን አለማወቅ፤ ከማንነታችን በታች እንድንሆን ያደርገናል" መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ
    መጋቢ ሔኖክ ዓለማየሁ፤ በሜልበርን ቤተ እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ፤ ለሕትመት አብቅተው እሑድ ሕዳር 8 / ኖቬምበር 17 ለምርቃት ስላሰናዱት "እኔ ማነኝ?" መፅሐፋቸው ዋነኛ ጭብጦች ይናገራሉ።
    13 November 2024, 4:48 am
  • 7 minutes 15 seconds
    አውስትራሊያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር ዝግጁ መሆኗን ገለጠች
    የአፍሪካ ኅብረት በአዲሱ የሰላም አስከባሪ ኃይል የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚያከብሩ አገራት ብቻ ይሳተፋሉ አለ
    12 November 2024, 10:19 pm
  • More Episodes? Get the App
© MoonFM 2024. All rights reserved.